Tuesday, November 5, 2013

በሸራሮ ከተማ ነጋዴዎችና በከተማዋ መስተዳድር አካላት መካከል የነበረውን ግንኝነት እየሻከረ በመምጣቱ መግባባት በማይችሉበት ደረጃ ላይ ይገኛሉ፣




በሸራሮ ከተማ በንግድ ስራ ተሰማርተው የሚገኙ ነጋዴዎች በመንግስት የሚጣልባቸውን ከሚያገኙት ገቢ ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብርና የመዋጮ ዓይነት ምክንያት ድርጅቶቻቸውን እስከ መዝጋት ደርሰዋል፣ የከተማዋ መስተዳድር ጥቅምት 22,2006 ዓ/ም በጠራው ስብሰባ የከተማይቱ ነጋዴዎች ተደራጅተው የሚሰሩ ከሆነ መንግስት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ ነው በማለት ላቀረቡት ሃሳብ ነጋዴዎቹ ዛሬም ሆነ ነገ በአንድ ድርጅት ስር ተደራጅተን ለመንቀሳቀስ ዝግጅዎች አይደለንም ሲሉ ገልጸዋል፣
ነጋዴዎች በመቀጠልም የቀረበላቸውን የመደራጀት ጥያቄ መንግስት በነጋዴው ላይ ከፍተኛ ግብር እየጣለ ገንዘባችንን እንዳልዘረፈ ሁሉ አሁን ደርሶ ከተደራጃችሁ  እናንተን ለመርዳት ዝግጁ ነኝ ማለቱ ነጋዴውን ለመጥቀም ሳይሆን በስመ ድርጅት ነጋዴውን ይበልጥ ለመቆጣጠር ካለው ፍላጎት ነው ሲሉ ህሳቡን ተቃውመውታል፣