የስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች በመቐለ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶችን ከስራ ቦታቸውና ከየመንገዱ ለስራ ትፈለጋላችሁ
በሚል ሰበብ በጸጥታ ሃይሎች በማሰባሰብ መንግስት የውትድርና ሞያ መጀመሩንና ለመመልመል ፈቃደኛ የሚሆኑ ወጣቶችን የተለያዩ ሞያዊ
ስልጠና እንደሚሰጣቸውና ተግባራዊነት የሌላቸው በርካታ ተስፋዎችን በመደርደር በወጣቱ ላይ ጫና በማድረግ ለውትድርና እንዲመለመል
እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ቷውቋል፣
የከተማዋን ወጣቶች በማስፈራራት ወደ ውትድርና እንዲገቡ እያደረጉ ካሉት አንዱ ም/ኮምሽነር ኪሮስ አብርሃ
ሲሆን እሱ ጥቅምት 12,2006 ዓ/ም ከ 200 በላይ የሚሆኑ ወጣቶችን በግዳጅ በማሰባሰብ እዚሁ ከተማ ካሁን ብሁዋላ የሆነ የስርቆት
ተግባር ወይም በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጾታዊ አመጽ ቢከሰት ወንጀለኛ ለመሆናችሁ ሌላ ማስረጃ አያስፈልገንም በማለት እንዳስፈራራቸው
የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣