የጸለምቲ ወረዳ መስተዳድር በወረዳው የሚገኙ አርሶ አደሮች ማዳበሪያ እንዲገዙ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ
ላይ ቆይቷል ፣ ነገር ግን ገበሬው መንግስት በ 2005 ዓ/ም ማዳበሪያ በውድ ዋጋ እንድንገዛ ማስገደዱ እንዳይበቃ አሁን ደግሞ
በመጋዘን ውስጥ የቆየ በትርፍ የመጣ ማዳበሪያን ለመሸጥ ሲል በገበሬው
ላይ ጫና ማድረጉ ተገቢ አይደለም ሲሉ ተቋውመውታል፣
የስርዓቱ ካድሬዎች ጥቅምት 19,2006 ዓ/ም የወረዳዋን ገበሬዎች ሰብስበው ጫና በማድረግና በማስፈራራት
ማዳበሪያውን ለመሸጥ ቢሞክሩ ህዝቡ በአንድ ድምጽ ድርጊቱን አውግዘውታል፣
በሁኔታው ቅር የተሰኘው የመድረኩ መሪ አቶ ማሞ አሸናፊ ፤ አቶ አስማረ አለበል ፤ ወ/ሮ ህይወት ታከለና
ወ/ሮ አጸደ ገ/መስቀል የሚገኙባቸው በርካታ ሰዎችን ጸረ-ልማትና አድመኞች በሚል ሰበብ እንዳሳሰራቸው ታውቋል፣