Wednesday, November 27, 2013

በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ልዩ ስሙ አልመሽ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኙ የጣና በለስ ፋብሪካ ሰራተኞች። ደመወዛቸው ሳይቆረጥ በግዜ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ከአካባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት እነዚህ በኣማራ ክልል ኣዊ ዞን። ጃዊ ወረዳ። ልዩ ስሙ ኣልመሽ ተብሎ በሚጠራ ኣካባቢ የሚሰሩ የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የቀን ሰራተኞች። የሰሩበትን ደመወዝ በማያውቁት መንገድ መቆረጡን ገልጸው። ጉዳዩን መፍትሄ እንዲደረግለት ለሚመለከተው ባለስልጣን እየጠየቁ መሆናቸው ሊማወቅ ተችለዋል፣
     ይህ በእንዲህ እያለ እነዚህ በስኳር ፋብሪካው የሚሰሩ ሰራተኞች። በአካባቢው ያለው የህክምና ማእከል ብቁ የሆነ አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ በወባ ወረርሽኝ በሽታ እየሞቱ ያሉ ሰራትኞች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመሄዱ። መፍትሄ ለማግኘት ለሚመለከተው ባለስልጣን ለአቶ አይናዲስ በተደጋጋሚ ጥያቄያቸውን አቅርበው። እስካሁን ድረስ መልስ እንዳልተሰጣቸው ዘገባው አክሎ ያስረዳል፣