በደረሰን ዘገባ መሰረት።
በምስራቅ ትግራይ ዞን ውቅሮ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የዓረና ፓርቲ አባላት። በህወሓት ካድሬዎች በደል እየደረሰባቸው ሲሆን። ዓረና
የጠራው ስብሰባም በህወሓት ካድሬዎች ደንቃራ ምክንያት እንደታወከና። በዚህም የዓረና አባል ለሆነው ይልማ ይኩኖ የተባለ አስተምሪ።
መታወቂያ ወረቀት ተጠይቆ ይዞ ባለመቆየቱና ማሳየት ባለመቻሉ ብቻ። ማንነቱ የማይታውቅ በሚል ሰበብ ከደበደቡት በኋላ። የህወሓት
ካድሬዎች አስተማሪውን ለብቻው በማሰር። ግፍ በተሞላበት የምርመራ
ሂደት። በኤሌትርክ ቶርች እንዳሰቃዩትና ሰውነቱ በሙሉ እንዳቆሰሉት ከቦታው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣
አቶ ይልማ ይኩኖ በመምህርነት ሞያ በማይጨው ከተማ የሚሰራ ሲሆን ።
የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬዎች በውቅሮ ከተማ ለሚገኘው የዓረና ፅሕፈት ቤት ለማስዘጋት እንዲመቻቸው በማለት ቤት ላከራየው ዜጋ በማስፈራራትና
የኪራይ ውልን በማፍረስ የድርጅቱን ጽ/ቤት እንዲዘጋ አድርገዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በትግራይ ክልል ፤በሰሜናዊ ምእራብ ዞን። በሽሬ-እንዳስላሰ
ከተማ ቀበሌ 01 ቄራ አካባቢ የሚገኙ መኖርያ ቤቶች። በከተማው ከንቲባ ትእዛዝ እየፈረሱ ሲሆን ይህ የመኖርያ ቤቶችን የማፍረስ
ተግባር ወደ ቀበሌ 02 እና 04 የሚቀጥል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣