በአማራ ክልል በምእራብ
ጎጃም ዞን፤ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከህዳር 10/2006 ዓ.ም ጀምሮ በፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪ ህዝብ ላይ አሰቃቂ በደል እየፈፀሙ
መሆኑን ዘገባው አመልክቶ ። የመንግስት ሰራተኘወችና ነጋዴዎች የሚገኙባቸው የከተማ ነዋሪዎች። እለታዊ ስራቸውን ሰርተው በሰላም
መግባት
እንዳልቻሉና ስጋት ላይ መውደቃቸው ለማወቅ ተችለዋል፣
እነዚህ እስከ አፍንጫቸው የታጠቀው የፌደራል ፖሊስ አባላት። በተለይም
ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምረው ሴቶችንና ህፃናት ልጆች በሚገኙበት መኖርያ ቤት አካባቢ እየዞሩ። በነዋሪው ላይ የተለያየ አላስፈላጊ
እንቅስቃሴዎች በማሳየት። ህዝቡን በማስፈራራትና በማሸበር ስራ ተሰማርተው እንዳሉ። ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣
በመጨረሻ የከተማው ነዋሪ ህዝብ በታጠቁ የስርአቱ ሃይሎች እየደረሰበት
ያለውን የሽብር ተግባራት እንዲቆም ለሚመለከታቸው የፌደራል ባለ ስልጣናት ቢያመለክትም እስካሁን ድረስ የተሰጠ መፍትሄ የለም፣