በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ
ዞን። በሽሬ ከተማ የሚኖረው ህዝብ እንደ ስኳር፤ ዘይት የመሳሰሉትና ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ኣላቂ ነገሮች። ህዝቡ በሚገዛበት የስርኣቱ
ማከፋፈያዎች ሊገኙ ባለመቻላቸውና፤ በንፁህ ውሃና መብራት ሃይል እጥረትም ለከባድ ሽግር እንደተጋለጡ፤ በተለይ ባለ ትላልቅ ድርጅቶች
የውሃ እጥረትና መብራት ሃይል በማጣታቸው በየእለቱ ኪሳራ ውስጥ ከመግባታቸው ባሻገር። ተገቢ ጥናት ባልተደረገበትና ወገናዊነት ኣሰራር
በተጠናወተው የግብርና የቀረጥ ክፍያ ተቸግረው እንዳሉ። ከከተማው የተገኘው መረጃ ኣስረድተዋል፣
ካከባቢው ሳንወጣ በሸራሮ ከተማ ከ300 በላይ የሚሆኑ በዲግሪ የተመረቁ
ተማሪዎች። ተመርቀው የሚሶሩበት ቦታ በማጣታቸው የሃገርና የቤተሰብ ተጠዋሪ ሆነዋል ያለው ይሀው መረጃ። በድንጋይ ንጣፍ ስራ ላይ
ተሰማርተው እለታዊ ንሮኣቸው እንዳይገፉ። ስርኣቱ ለይምሰል ለኣርባ ቀናት ስልጠና ቢሰጣቸውም። በስልጠና ማጠቃለያ ላይ። ከተሰጣቸው ትምህርት ተያያዥነት የሌለው ፈተና በማቅረብና ሁሉንም እንዲወድቁ
በመደረጉ። ሰልጣኞቹ ባካባቢው ኣስተዳደር ላይ ተቃውሞ ስላስነሱ።
ከባድ ውጥረት ሰፍኖ እንዳለ ምንጮች ከቦታው ገለፁ፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሸራሮ ከተማ ውስጥ።l ለህዝብ ማህበራዊ ኣገልግሎት
የሚውል ዘይትና ሱካር የመሳሰሉት ከገበያ ጠቅልለው ስለጠፉ። ህዝቡ ተቸግሮ እንዳለና ችግሩ ቢገልፅም ሰሚ ጀሮ እንዳላገኘ ለመረዳት
ተችለዋል፣