Sunday, December 1, 2013

በኣማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ለሚገኘው ዩንቨርስቲ ተብሎ የሚመደብ በጀት። በትምህርት ቤቱ ኣስተዳዳሪዎች እየባከነ እንዳለ። የዩንቨርስቲ ተማሪዎቹ ጥቅምት 12/2006 ኣ.ም በሰጡት መረጃ ሊታወቅ ተችለዋል፣



በመረጃው መሰረት በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ የሚገኙ ተማሪዎች። ለተማሪዎች ቀለብ ተብሎ በመንግስት ለተመደበ በጀት። በዩንቨርስቲው ኣስተዳዳሪዎች እየተመዘበረና። በተማሪዎቹ ቁጥር መሰረት ተደርጎ ከተፈቀደላቸው 80 ኪሎ ስጋ። በግማሽ ተቀንሶ 40 ኪሎ ብቻ ሊገዛ በማድረግ። የተቀረው ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት ኣንዳሉ ተገለፀ፣
      የይንቨርስቲው ተማሪዎች ለትምህርት ቤቱ የመጣው በጀት በትክክል እልተጠቀምንበትም በሚልና። የኣስተዳዳሪዎቹ ቅጥ ያጣ ብልግና በመቃወም። በጥቅምት 12 2006 ኣ.ም ለሚመለከታቸው ባለ ስልጣናት ቅሬታቸው ቢያቀርቡም። ቅሬታው የተቀበሉት          ባለ ስልጣኖች ከባከነው ገንዘብ ተካፋዮች በመሆናቸው። ተገቢ መልስ እንዳልሰጡበትና። ተማሪዎቹ እስካሁን ድረስ ብሶታቸው እየገለፁ መሆናቸው መረጃው ኣክሎ ኣስታውቀዋል፣
     በብልግና ኣይናቸው ማየት የተሳነው የዩንቨርሲቲው ኣስተዳዳሪዎች። ከቀይ መስቀል ለትምህርት ቤቱ ተብሎ በእርዳታ የተገኘው ብርድ ልብስ። ወደ ተማሪዎች እጅ ሳይገባ ኣየር በኣየር ሽጠው ለጥቃማቸው እንዳዋሉት የገለፀው ይሀው መረጃ። ይህን ኣልበቃ ብሎዋቸው ከያንዳንድ ተማሪዎቹ ኣስር ኣስር ብር ተዋጥቶ የተገዛችው የህሙማን ማመላለሻ ኣምቡላንስ። ባለስልጣኖቹ ልግል ጥቅማቸው እየተገለገሉባት። እንዳሉ ከኣካባቢው በተገኘው መረጃ ሊታወቅ ተችለዋል፣