እነዚህ በፌደራል ፖሊስ
ሃላፊነት የጎደለው ግፍ እየደረሰባቸው ያሉ ዜጎቻችን። በስልጣን ያለው ፀረ ህዝብ መንግስት። በምእራብ ትግራይ ዞን ስራ ኣለ ብሎ
በማወጅ። ከተለያዩ ያገራችን ኣካባቢዎች ላመጣቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የቀን ሰራተኞች። ለተቃዋሚ ድርጅቶች እየተባበራቹህ ነው በሚል
ሰንካላ ምክንያት። በላያቸው ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ መረጃው ኣስረድተዋል፣
መረጃው ጨምሮ በተለይ በማይ ካድራ፤ ሉጉዲ፤ ባናትና ኣውደራፍእ በተባለ
ኣካባቢ። በቀን ስራ ውስጥ ለተሰማሩ ሰራተኞች ብፌደራል ፖሊስ ተገድው ኣንድ ቦታ ላይ እንዲሰበሰቡ ከተደረገ በሃላ። ወደዚህ የመጣቹህ
ልትሰሩ ሳይሆን። ትጥቃዊ ትግል ከምያካሂዱ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ለመተባበር ነው በሚል መሰረት የሌለው ምክንያት። በላያቸው ላይ
ድብደባና እንግልት እያደረሱባቸው መሆኑን ታውቀዋል፣
ይህ በንዲህ እንዳለ። በሁመራ ከተማ ውስጥ ኣውቶብስ መናሃርያ ኣካባቢ የሚገኙ። ልብስ በመሸጥና ቁርስ ቤት ከፍተው በመተዳደር ላይ ለነበሩ
ባለ ድርጅቶች። በህዳር 17 2006 ኣ.ም የስርኣቱ ካድሬዎችና የፀጥታ ሃይሎች ባንድነት ተባብሮው። ከሚሰሩበት ድርጅት በማባረር።
ከነ ንብረታቸው በማሃል ሜዳ ላይ ስለ ጣልዋቸው። ለከባድ ብርድና ፀሃይ እንደተጋለጡ፤ ኣጠቃላይ የከተማው ነዋሪም በንፁህ የሚጠጣ
ውሃ እጥረት እየተሰቃየና። ለኣንድ በርሜል ውሃ በ 30 ብር ሂሳብ። ጥራቱ ካልጠበቐ የተከዜ ውሃ በማስመጣት እየተጠቀመ በመሆኑ።
በርከት ያሉ ነዋሪዎች በውሃ ወለድ በሽታዎች ተጠቅተው። ስቃይ ላይ
እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ ኣስታውቀዋል፣