Friday, December 6, 2013

ከሳዉዲ አረብያ ተፈናቅለዉ የተመለሱ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን። ነፃ ከሆኑ ጋዜጠኞችና ሚድያዎች ጋር እንዳይገናኙ ክትትልና ጥበቃ እየተደረገባቸዉ መሆኑ ተገለፀ፣




እነዚህ በግዝያዊ ማቆያ ኣንዲያርፉ በአዲስ አበባ በሚገኝ የኢምግሬሽንና የሲቭል ሰርቪስ አዳራሾች ዉስጥ ተዘግተዉ ያሉ ዜጎቻችን። ከቦታ ወደቦታ እንዳይንቀሳቀሱና ከማንም ሰዉ ጋር እንዳይገናኙ ሌትና ቀን በጸጥታ ሃይሎች እየተጠበቁ ባሉበት ግዜ። ካረፉበት አዳራሽ ወጥተዉ ለመገባየትና ስልክ ለመደወል ቢፈልጉም እንኳን። በፀጥታ ሃይሎች ፍቃድ ካልሆነ በስተቀር። በገዛ ራሳቸዉ ወጠው ሲንቀሳቀሱ ለተገኙ በላያቸዉ ላይ ከባድ ማስጠንቀቂያና ማስፈራርያ እየወርደባቸዉ መሆኑን ለአይን እማኞች መሰረት በማድረግ ከቦታዉ የደረሰን መርጃ አስረድትዋል፣
   መረጃዉ እንደሚያመለክተዉ። በስልጣን ላይ ያለዉ የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት። ለተመላሽ ወገኖቻችን በቂ በጀት መድቦ አስፈላጊዉን እርዳታ እያደረገላቸዉ ኣንዳለ በተደጋጋሚ በራሱ ሚዲያዎች እየገለፀ ቢሆንም። ነገሩ ተግባራዊነት የሌለዉ ተራ ፕሮፖጋዳ መሆኑንና። ተፈናቃዮቹ ወደ ትዉልድ ሃገራቸዉ ሲሄዱ ለትራንስፖርት ተብሎ ዘጠኝ መቶ (900) ብር ብቻ ስለሚሰጣቸዉ ትዉልድ ቦታቸዉ ከደረሱ በኋላ ለስራ መጀመሪያ የሚሆን ገንዘብ ስለማይሰጣቸዉ ለከፋ የአእምሮ ጭንቀት ተጋልጠዉ ኣንዳሉና ይህንን በተመለከተም ለማነኛዉም የነፃ ሚዲያዎች። መረጃ እንዳይሰጡ በፅኑ እየተጠበቁ መሆናቸዉን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣