ይህ በፉኖተ-ሰላም አዳራሽ ‘ከመጋቢት 8 እስከ 28 /2006 ዓ.ም በመካሄድ ላይ የሚገኘው የውይይት መድረክ
ከ20 ቀበሌዎች የተወጣጡ 200 የሚሆኑ አመራሮች የሚሳተፉበትና በከፍተኛ የአማራ ክልል አመራሮች የሚመራ መድረክ እንደሆነ የገለፀው
መረጃው ወደ ስብሰባው ይዘውት የቀረቡት አጀንዳ አብዛኛው በተሳታፊዎቹ
ተቀባይነት እንዳላገኘ ለማወቅ ተችለዋል።
ስብሰባውን የመሩት የአማራ ክልል ከፍተኛ
አመራሮች 2007 ለሚካሄደው ምርጫ የናንተ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው የሚሉ እና ሌሎች ተዛማጅ ሃሳቦች ያቀረቡላቸው ሲሆን፣ በተሳታፊዎች የቀረበ ሃሳብ ግን-
1. ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን ከተፈለገ ኢህአዴግ ለምን ብቻውን ቅስቀሳ ያደርጋል?
2. የ5 አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሚሽኑ እቅድ ለማሳካት ሲባል ለገበሬው እየቀረበ ያለው
የማዳበርያ ዋጋ ጣርያ ደርሶ ህዝቡ እያማረረ ነው?
3. ህዝባችን በአፈርና ውሃ ጥበቃ፤ በማዳበርያ ብድርና የጤና ፓኬጅ አልተሳተፍክም እየተባለ በመሰቃየት ላይ
ስለሆነ ነገ ጥዋት ‘ምረጠን በምንልበት ግዜ ሊመርጠን አይችልም?
ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ሃላፊነት አንወስድም እንዳሉ ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማውቅ ተችልዋል።
በተመሳሳይ ከዚሁ ዞን ሳንወጣ ቡሬ ወረዳ
ፈዚል፤ ሶንቶም፤ ቦቆጣቦ ዘልማ ቀበሌዎችና በአዊ ዞን ባንጃ ወረዳ
ሱርታ በሚባል አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች የወሰዳችሁትን ብድር አልመለሳችሁም፤ ለመልስ ፋውንዴሽን የሚሆን ገንዘብ አልከፈላችሁም እየተባሉ
ከብቶቻቸው በስርዓቱ ካድሬዎች ከበረታቸው እየተወሰዱባቸው እንደሆነ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድተዋል።