በደረሰን መረጃ መሰረት
በስልጣን ላይ ያለው ገዢ መንግስት መላዉ የባህርዳር’ና የሊበን ህብረተሰብ የጤና መድን አባል መሆን አለበት የሚል ተደጋጋሚ ሓሳብ ሙሉ በሙሉ ያልተቀበለው መሆኑ የጠቆሞው መረጃው የእነዚህ
ከተሞች አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች እንደ መሳርያ ሊጠቀሙባቸው ያደራጁትን አንድ ለአምስትና ሰባት ለሳላሳ የሚሉዋቸው አሰራር ተጠቅመው ነጋ ጠባ ስብሰባ እየጠሩ አስገድደው አባላት ሁኑ እያሉ
ትእግስታቸው እያስጨረሱዋቸው እንዳሉ አስረዱተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በባህርዳር እየተካሄደ በነበረው የመላው የኢትዮጵያ
ስፖርት ዉድድር የተሰየመው ጨወታ ብዛት ያለው ህዝብ ወደ ከተማዋ በመግባቱ ምክንያት በባህርዳር’ና በአካባቢው የሚገኙ የሊበንና
ሌሎች ከተሞች የኑሮ ዉድነቱ አባብሶት እንደሚገኝና በተለይ ሆቴሎችና የአላቂ ሸቐጦች ዋጋ በመናሩ ምክንያት የዞን ነዋሪ ህዝብ እለታዊ
ኑሮዉን ለመምራት እንደተቸገረ ለማወቅ ተችለዋል።
መረጃው በመጨረሻ እንደገለጸው ህዝባዊ አመለካከት የሌላቸው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ
ስርአት መሪዎች ለጤና መድን፤ ለመለስ ፍዉዴሽንና ለሌሎች ጉዳዮች ማስፈፀሚያ በማለት ህብረተሰቡን ገንዘብ ክፈል እያሉ ቢያስቸግሩትም
ህዝቡ የሚጠየቀውን ገንዘብ ሊከፍል አቅም እንደሌለው በምሬት በመግለፅ
ላይ መሆኑ የተገኘው መረጃ አመልክተዋል።