የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት
በልማት ስራ ወቅት አልመጣቹሁም፤ ለልማት ስራ የሚውል ገንዘብ አላዋጣችሁም፤ ህዝቡ በገዘቡና በጉልበቱ አገሩን እንዳያለማ ያልሆነ
ቅስቀሳ በማድረግ አቅጣጫውን እንዲስት ታረጋላቹህ በማለት ንፁሃን ወገኖችን ለማሰር እንደ ብልሃት እንደሚጠቀምበት የተገኘው መረጃ
አስታወቀ።
ከታሰሩት የተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት ውስጥ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ
ከሚንቀሳቀሱ የ.መ.ኢ.አ.ድ አመራር አቶ አለምየ ጫኔ፤ አቶ ሞላ ገረሞውና ሌሎች ስማቸው ያልተጠቀሱ እንደሚገኙባቸውና የተቃዋሚዎች
መታሰርም በሰላማዊ መንገድ ስርአቱን ስለተቃወሙት ብቻ እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ ክልል አላማጣ ከተማ ውስጥ ታስረው ከሚገኙ
የተቃዋሚ ድርጅት አባላት አንዱ የሆኑ አቶ እያሱ ሁሴንና አዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አራት የድርጅቱ አመራር
መታሰራቸውን የገለጸው መረጃው በኦሮምያ ክልል ኪረሙና ነቀምት ዞን የሚገኙ የተቃዋሚ አባላትም በሃሰት ተከሰው እየታሰሩ መሆናቸውን
መረጃው አክሎ አስረድተዋል።