በመረጃው መሰረት የማዕከላዊ
ዞን አስተዳዳሪዎች በአድዋ ከተማ አካባቢ የሚገኘውን የእርሻ መሬት
ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር ምንም አይነት መረዳዳትና የካሳ ክፍያ ሳያደርጉ እየቀሙ ወደ ከተማ አስተዳደሩ እያስገቡት ሲሆን አርሶአደሮቹ
በበኩላቸው ፍትህ ለማግኘት ወደ አስተዳዳሪው በመሄድ ያቀረቡት አቤቱታ ሰሚ ማግኘት እንዳልቻሉ ተገለፀ።
በዚህ እየተፈፀመ ባለው ሃላፊነት በጎደለው የስርዓቱ አሰራር የተቆጡ ከ1300
በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ሚያዝያ 14 /2006 ዓ/ም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን የጠቀሰው መረጃው በአርሶ አደሩ ተቃውሞ
ስጋት ያደረባቸው የከተማዋ ባለስልጣናት ፖሊስ በመላክ ሰልፉ እንዲበተን ማድረጋቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።