Wednesday, May 14, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የማይ-ካድራ ከተማ የቀበሌ አስተዳዳሪ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት እንደሞተ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይካድራ ከተማ የቀበሌ አስተዳዳሪ  የሆነው አቶ ጎሹ አሰፋ ሚያዝያ 28 2006 ዓ/ም ከረዳቶቹ ጋር ወደ ማይካድራ በረሃ ልዩ ስሙ በሸር ወደ ተባለ የእርሻ ቦታ በመሄድ መሬት መሸነሽን ሲጀምር ማንነታቸው ባልታወቁ ዜጎች በተተኮሰ  ጥይት ተመትቶ እንደሞተ መረጃው አስረድቷል።
  ይህ ፍፃሜ በተመሳሳይ በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች እየቀጠለ መሆኑን በዜና እወጃችን እየገለፅን መቆየታችን  ይታወሳል።