በመረጃው መሰረት ስብሰባውን
ይመሩ የነበሩት አመራሮች የተለመደውን የስርዓቱ የይምሰል አካሄድ መስበክ ሲጀምሩ በተሰብሳቢዎችና
በአመራሮች መካከል ከዚህ በፊት ክፍተት ስለነበርና አሁንም ሊረዳዱ እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ በመነሳትም ነዋሪዎች ሚያዚያ 23 /2006 ዓ/ም ወደ ተቃውሞ ሰልፍ
እያመሩ በነበሩበት ሰዓት የፌዴራል ፖሊስ መለዩ የለበሱና ከአዲስ አበባ የመጡ የአግኣዚ ኮማንዶዎች በከፈቱት ተኩስ ከ7 በላይ ሰልፈኞች
እንደሞቱ መረጃው አክሎ አስረድቷል።
እንደሚታወቀው የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት አሁን ተጀምሮ እንዳለው ህዝባዊ
ማዕበል ሲቀሰቀስ አግኣዚ የተባሉ የኮማንዶ አሃዱዎችን በማሰማራት ህዝብ እንደሚጨፈጭፍና ከ1997 ዓ/ም ምርጫ ጀምሮ እየተፈፀመ
ያለው አረመኔያዊ ተግባራቱ መሆኑ ይታወቃል።