Wednesday, May 14, 2014

በሰሜን ዕዝ ቡሬ ግንባር የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የ7 ዓመት አገልግሎታችንን ስለጨረሰን ወደ ቀያችን አሰናብቱን ዳግመኛ ለማገልገል አንፈርምም በማለት ተቃውሞቸውን እየቀጠሉ እንዳሉ ታውቋል።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በቡሬ ግንባር የሚገኙ ከፍተኛ መኮነኖችን ያካተተው በርካታ የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በስርዓቱ ያላቸው እምነት እየቀነሰ በመሄዱና ወታደራዊ ህይወትም በተበላሸ አሰራር ምክንያት እየመረራቸው ስለሆነ ወደ አገራችን ስደዱን እያሉ በተደጋጋሚ አድማ እያስነሱ መሆናቸውን አስረድቷል።
     በዚህ መሰረትም ሰራዊት አነሳስታችኋል በሚል ምክንያት በርካታ የሰራዊቱ መኮነኖች ታስረው እንዳሉና የዕዙ ከፍተኛ ሃላፊዎችም ይህ ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ ማነኛውም ሰራዊት ወደ ቤተሰብ በፈቃድ እንዳይሄድና ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ መከልከላቸውን መረጃው አክሎ አስታውቋል።