Wednesday, May 14, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ የሚገኙ ስራ ፈላጊ የሆኑ ወገኖቻችን የተቃዋሚ ድርጅቶች ተላላኪ ናችሁ እየተባሉ በኢህአዴግ ካድሬዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አመለከተ።



እነዚህ በሁመራ ከተማ  ልዩ ስሙ መስቀል አደባባይ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የከተማዋ ፖሊሶች በመሄድ በስራ ፈላጊ ዜጎቻችን ላይ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተላላኪዎችና ሌቦች ናችሁ እያሉ በማስፈራራት ሚያዝያ 28/2006/ዓ.ም ሰብስበው ወደ እስር ቤት በመውሰድ አስረው እያሰቃዩዋቸው እንዳሉ ተገለፀ።
     ከ160 በላይ የሚሆኑ ስራ ፈላጊ ዜጎቻችን የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖራቸው ሁመራ ውስጥ በሚገኙ በስርዓቱ የፖሊስ አባላት ወደ እስር ቤት ተወስደው ታጎረው እየወረደባቸው ያለው ግፍና ስቃይ እንዲቆም ለሚመለከታቸው  የመንግስት አካላት አቤቱታ ቢያቀርቡም ችግራቸውን ሰምቶ ምላሽ የሚሰጥ ባለስልጣን ማግኘት እንዳልቻሉ የገለፀው መረጃው ለዚህ አስነዋሪ ተግባር እየፈፀሙ ካሉት የስርዓቱ ተላላኪ ካድሬዎች መካከልም አብረሃ የተባለው የሁመራ ከተማ የፀጥታ ሃላፊ እንደሆነ  ሊታወቅ ተችሏል።