Friday, May 16, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ውስጥ በተለያየ ምክንያት ወላጆቻቸው የሞቱባቸው አሳዳጊ ያጡ ወገኖች የወላጆቻቸውን መሬት የመውረስ መብታቸውን እንደተከለከሉ ከቦታው የተገኘው መረጃ ገለፀ፣፣



በመረጃው መሰረት በቃፍታ ሁመራ ወረዳ ቤተሰባቸውን በሞት ምክንያት የተለዩዋቸውና ያለ አሳዳጊ የቀሩት ወገኖቻችን የወላጆቻቸውን መሬት ወርሰው እንዳይጠቀሙና ኑሮአቸውን እንዳይመሩ በአካባቢው አስተዳዳሪዎች ተከልክለው ለከባድ ችግር መጋለጣቸው ታወቀ፣፣
    እነዚህ በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸው የሞቱባቸውና መሬት እንዳይወርሱ ተከልክለው በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችን በላያቸው ላይ የወረደውን ኢ-ፍትሃዊ አሰራር እንዲስተካከልላቸውና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው በማለት ወደሚመለከታቸው የዞንና የወረዳው አስተዳዳሪዎች በመሄድ ብሶታቸውን ቢያቀርቡም የወረደው መመርያ ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ስለሆነ የምናውቀው ነገር የለም  የሚል መልስ ስለሰጥዋቸው በስርአቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ይበልጡን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን መረጃው አስታውቀዋል፣፣