Sunday, May 11, 2014

ህወሃት ማሌሊት በትግራይ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ለ2007 ዓ/ም ምርጫ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ በማለት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ባጀት በመመደብ ለማሰናከል እየሰራ መሆኑን ተገለጸ።



በመረጃው መሰረት ይህ የወያኔ ኢህአዴግ ተግባር በሁሉም የአገራችን ክፍሎች ስርአቱ የሚሰራበት መሆኑና በተለይ ደግሞ በትግራይ የአረና ፓርቲ አባላት ለሆኑ ወጣቶች ለሚመጣው ምርጫ ላመኑበት ድርጅት ደግፈው ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ በገንዘብ ብዛት እያታለሏቸው እንዳሉና አንታለልም ላሉት ደግሞ ከያዙት አላማ እንዲያፈገፍጉ ለማድረግ እያስፈራሯቸውና እያሰሯቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው በማከል ተቃዋሚ ድርጅቶች ሃይላቸውን አጠናክረውና ህዝባዊ ድጋፍ አግኝተው በሚመጣው የ2007 ዓ/ም ምርጫ ላይ እንዳይሳተፉና እንዲበታተኑ በሃላፊነት ደረጃ ላይ ሆኖ ተንኮል እየጎነጎነ ያለው የወያኔው ካድሬ ወልዱ (ወዲ አድዋ) እየተባለ የሚጠራው የቀድሞ ታጋይ መሆኑን መረጃው አስረድተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወሃት ኢህአዴግ ስርአት የሰራዊት አዛዦች በተለይ ደግሞ የትግርኛ ተናጋሪዎች በሃገራችን ከተሞች የሲቪል ልብስ ለብሰው ወጣቶችን የተቃዋሚ ድርጅት አባላቶች ናችሁ እያሉ እያሰሩና እያስፈራሩ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።