Sunday, May 11, 2014

በሰሜን ጎንደር ዞን አብደ-ራፍዕ የሚገኙ የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት የዜጎችን መታወቂያ ወረቀት በመቀማት እየቀደዱ መሆኑን ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት በአብደ-ራፍዕ ከተማና አካባቢው የሚገኙ የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ አባላት የዜጎችን የመታወቂያ ወረቀት በሃይል እየቀሙ መቅደዳቸውን የገለፀው መረጃው በዚህ ምክንያትም ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ዕለታዊ ስራቸውን መስራት ባለመቻላቸው በስርዓቱ ያላቸውን ጥላቻ እየገለፁ  እንደሚገኙ ታውቋል።
  ነዋሪዎችም በታጠቁት ሃይሎች እየተፈፀመ ያለውን ከህጋዊነት የራቀ አሰራር መፍትሄ እንዲደረግለት ወደ ሚመለከታቸው አካላት በመሄድ አቤቱታ አቅርበው የተሰጣቸው ምላሽም “2007 ዓ/ም የሚካሄደውን ምርጫ ምክንያት በማድረግ አዲስ የመታወቂያ ወረቀት ሊሰጥ ስለሆነ ይህን ያላደረገ ደግሞ ኣንደዜጋ አይቆጠርም በማለት እንደአስፈራሯቸው ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።