ሚያዝያ 17/2006 ዓ/ም በመተማ አካባቢ ሽንፋእ በተባለ በረሃ በፌድራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት አባላት
መካከል በተቀሰቀሰ ተኩስ ከ50 በላይ እንደሞቱና በርካታዎች እንደቆሰሉ
የገለፀው መረጃው የተኩሱ መነሻም በስርዓቱ ምክንያት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ዕለታዊ ኑሮአቸውን መምራት ያልቻሉ የአካባቢው ነጋዴዎች
ሆን ብለው “የታጠቁ ተቃዋሚዎች። በዚህ አለፉ” የሚል የተሳሳተ መረጃ በመስጠታቸው መሆኑን ጨምሮ ገልጿል።
በተጨማሪም ይህን ቅንነት የሌለው መረጃ
የሰሙ የፌድራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት የታጠቁ የተቃዋሚ ሃይሎችን ለማጥቃት ሲንቀሳቀሱ ሁለቱም ባለማወቅ ተኩስ እንደከፈቱ
ከገለፀ በኋላ መልዕክቱን ለነገራቸው አቶ ሙሴ ይርጋ ለተባለ ነጋዴ ደግሞ አገዳደልህን በማለት አስረውት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።