በመረጃው መሰረት የደብረ-ማርቆስ
ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ያለው ብልሹ አሰራርና የሃገሪቱ
መንግስት ከስልጣን ይውረድ የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ሚያዝያ 28/2006 ዓ/ም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን የገለፀው
መረጃው በተነሳው የተቃውሞ ሰልፍና ግርግር በርካታ መኪናዎችና ንብረቶች እንደወደሙም ታውቋል።
ተቃውሞ ሲያካሂዱ የነበሩ ተማሪዎችም ለዩኒቨርሲቲው ዲን አንተ የስርዓቱ
ተላላኪና ለተቋሙ ተብሎ የተመደበ በጀት ለግል ጥቅምህ እያዋልከው
ስለሆንክ በመማር ማስተማሩ ላይ እንቅፋት ፈጥረሃል በማለት በገመድ አስረው ከግቢው ወደ ዋናው አስፋልት መንገድ እንዳወጡት መረጃው
ገልጿል።
በዚህ ፍፃሜ ስጋት ላይ
የወደቁ አስተዳዳሪዎችና የስርዓቱ ካድሬዎች ብዛት ያላቸው የፌዴራል ፖሊስ አባላት አሰማርተው ለተቃዋሚው በማገትና ተማሪዎችንም ሰብስበው
ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ እንዲገቡ ማስገደዳቸውን በመግለፅ ከግቢው ውስጥም እንዳይወጡ በማገድ ያለ ውሃና ምግብ ለ4 ቀናት ዘግተው በረሃብና በጥም ቢያሰቃዩዋቸውም እንኳን ግርግሩና
ተቃውሞው ግን አሁንም እየቀጠለ እንደሆነ ተውቋል’።
በተመሳሳይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ ወደ ሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በመዛመት
ግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ/ም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በስርዓቱ ላይ ተቃውሞ እንዳካሄዱና የነበረው ተቃውሞም በፌዴራል ፖሊስ
አባላት ሊበተን እንደቻለ ከስፍራው ምንጮቻችን አስረድተዋል።