በምንጮቻችን መሰረት
ብርሃነ ይርጋ የተባለው የቀበሌው አስተዳዳሪ የተሰው ሰማእታት መሬት
ለሌላ ሰው እናድለዋለን በማለት መሸነሽን እንደጀመረ ሌሊት በማን
እንደተተኮሰ ባልታወቀ ጥይት እንደተገደለ ይዞት የነበረው የመሬት
ሽንሸና መዝገብና የጦር መሳሪያ እንደተወሰደ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው አክሎ እንዳስረዳው “ለሕዝብና ለሃገር ብለው የተሰዉ ጀግኖች
መሬታቸውን ለልጆቻቸው ከመስጠት ይልቅ ቀምተው ለሌሎች ሰዎች መስጠታቸው ሚያሳዝን ነው ” ካሉ በኋላ የአከባቢው ካድሬዎች የሚያደርጉትን ተግባር ካላቛረጡ የተገደለው የቀበሌው አስተዳደር እጣ ፋንታ ሊደርሳቸው እንደሚችል
የእድሪስ ቀበሌ ነዋሪዎች እየተነጋገሩበት እንዳሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።