Friday, May 16, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ ወይን ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የእንጠጦ አምባ አስተማሪዎች የገንዘብ መዋጮ ለመክፈል አቅም የለንም በማለታቸው ብቻ፣ በኢህአዴግ ካድሬዎች ከስራቸው እየተባረሩ መሆናቸው ተገለጸ፣፣



በወይን ወረዳ እንጠጦ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚያስተምሩ 193 የሚደርሱ አስተማሪዎች ለህዳሴ ግድብ የሚውል ገንዘብ እንዲከፍሉ በተደጋጋሚ ተጠይቀው አቅም ባማጣታቸው ምክንያት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ለቀሩት 4 አስተማሪዎች፣ በስርአቱ ካድሬዎች ከስራቸው እንደተባረሩ ለማወቅ ተችሏል፣፣
    ይህ በእንዲህ እንዳለ የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ደመላሽ ነጋሪ የተባለው የስርአቱ ተላላኪ፣ ስልጣኑን መከታ በማድረግ የትምህርት ቤቱ የፕላዝማ ቴክኒሻን ለሆነው ደረጄ ለተባለው አስተማሪ በተደጋጋሚ ገንዘብ እንዲከፍል ተጠይቆ ፈቃደኛ መሆን አልቻለም በማለት  ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከስራው እንዳባረረው መረጃው ጨምሮ አስታውቋል፣፣