Tuesday, May 13, 2014

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተሰላምና የቡሬ ከተማ ነጋዴዎች ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ ስለ ተወሰነባቸው ድርጅቶቻቸውን እንዲዘጉ እየተገደዱ መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



እነዚህ በንግድ ስራ ተደራጅተው ቤተሰቦቻቸውን ሲያስተዳድሩ የቆዩ የፍኖተሰላም እና የቡሬ ከተማ ነዋሪዎች በአሁኑ ጊዜ ከአቅማቸው በላይ የሆነና ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ ስለ ተወሰነባቸው ድርጅቶቻቸውን እንዲዘጉ በመገደዳቸው ለኪሳራና ለድህነት መጋለጣቸውና በዚህ ምክንያትም  በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ላይ  ያላቸውን እሮሮና ምሬት እየገለፁ መሆናቸው ታውቋል።
    መረጃው ጨምሮም ከመጠን በላይ ግብር ተጥሎባቸው ግን ለመክፈል አቅም ስለሌላቸው ከተዘጉ ድርጅቶች መካከል።-
-    ሙሉ ሆቴል 95 ሺህ ብር
-    ደረጀ የአላቂ እቃዎች ማከፋፈያ 135 ሺህ ብር
-    አባይ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ማከፋፈያ 110ሺህ ብር እና ሌሎችም መሆናቸውን ጠቅሶ የእነዚህ ድርጅት ባለቤቶች እስከ ቤተሰቦቻቸው ችግር ውስጥ መውደቃቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣