Tuesday, May 13, 2014

በጎንደር ከተማ መኖሪያ ቤታቸው በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት የፈረሰባቸው ዜጎች ተቃውሞ በማሰማታቸው ምክንያት እየታሰሩ መሆናቸውን ከከተማው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ቤታቸውን ያፈረሰባቸው የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተለዋጭ ቦታና የካሳ ክፍያ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ህፃናትና አዛውንት የሚገኙባቸው በርከት ያሉ ቤተሰቦች በረሃ ላይ ተጥለው ለፀሓይና ለብርድ በመጋለጣቸው  ምክንያት የበሽታ ሰለባዎች መሆናቸውን የገለፀው መረጃው እነዚህ ወገኖች ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታ ቢያቀርቡም ፍትህ ሊያገኙ ባለመቻላቸው መንግስትን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ ተገለፀ።
  እነዚህ ቤታቸው የፈረሰባቸው ንፁሃን ዜጎቻችን ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሰልፍ በመግለጻቸው ብቻ በጎንደር ከተማ ውስጥ በሚገኙ እስር ቤቶች ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙና ከእነዚህም መካከል- አቶ መልካሙ ሲሳይ፤ አቶ ሰለሙን ገብረ መድህን፤ አቶ አህመድ ሁሴን፤ አቶ አበራና ሌሎችም መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።