Sunday, May 11, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን በወልቃይት ወረዳ የሰላም ቀበሌ አስተዳዳሪ የሆነው የስርአቱ ካድሬ መሬትን ለመሸንሸን ብሎ በሄደበት ግዜ ጥይት ተተኩሶበት እንደተሳተ ተገለጸ።



ይህ ሚያዝያ 16/2006 ዓ/ም ይሸነሸናል ተብሎ ለተወሰነው መሬት ለማጥናት ወደ ኣካባቢው የተንቀሳቀሰው አበባው ፀጋይ የተባለ የሰላም ቀበሌ አስተዳዳሪ ጥናት ሲያካሄድበት በነበረበት ቦታ ማንነታቸው ካልታወቁ ሰዎች ጥይት እንደተተኮሰበት ያገኘነው መረጃ አመለከተ።
    የሰላም ቀበሌ አስተዳዳሪ የሆነው አቶ አበባው ፀጋይ በላዩ ላይ ከተሞከረበት የጥይት እሩምታ ተኩስ ለጥቂት እንደተረፈና ከቦታው ሸሽቶ እንዳመለጠ  የጠቀሰው መረጃው ድርጊቱ ከተፈፀመ በኃላም በአካባቢው ትልቅ ፍርሃትና ግርግር በመስፈኑ ምክንያት የስርአቱ ፌደራል ፖሊስ ለማረጋጋት ቢሞኩሩም እስካሁን ድረስ ግን ጥይቱ የተኮሱትን ሰዎች ማወቕ እንዳልተቻለ መረጃው አክሎ አስረድቷል።