Friday, May 16, 2014

በትግራይ ማእከላዊ ዞን በታህታይ ማይጨው ወረዳ ነዋሪ ህዝብ ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል ምክንያት ፍትሓዊ ባልሆነ መንገድ በአስተዳዳሪዎቹ ገንዘቡ እየተመዘበረ መሆኑ ተገለጸ፣፣



በመረጃው መሰረት በሴፍት-ኔት ታቅፎ የሚገኘው ድሃው ህብረተሰብ፣ በየወሩ ሲከፍለው ከነበረው 90 ብር፣ ለመለስ ፋውንደሽን ተብሎ ከፍላጎቱ ውጭ 50 ብር በመቆረጡ ምክንያት ብሶቱን እያሰማ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል፣፣
    ይህ ለመለስ ፋውንዴሽን እየተባለ እየተሰበሰበ ያለው ገንዘብ ህዝቡን ለማስቸገር ካልሆነ በስተቀር፣ የሚሰጠው እርባናና ተስፋ የለውም ብለው እንደተቃወሙት የገለፀው መረጃው፣ የወያኔ ኢህአዴግ ባለ-ስልጣናት መለስ በሂወት እያለ ይመዝብሩን የነበረው ገንዘብ አልበቃ ብሎዋቸው ከሞተ በኃላም በስሙ እየነገዱ ናቸው በማለት በሰፊው እየተነጋገሩበት መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድተዋል፣፣