Sunday, May 18, 2014

ለበርካታ ወራት ሲሰለጥኑ የቆዩ የትህዴን ሰልጣኞች የድርጅቱ ሊቀመንበር በተገኘበት በደማቅ ሁኔታ ተመረቁ።



ለበርካታ ወራት ሲሰለጥኑ የቆዩ ብዛት ያላቸው የትህዴን ሰልጣኞች ግንቦት 7/2006/ዓ.ም የድርጅቱ ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶምና ሌሎችም የሰራዊት አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ መመረቃቸውን ሪፖርተራችን ከቦታው ገለፀ።
  ሓሙስ ግንቦት 7/2006/ዓ.ም እኩለ ቀን የተጀመረው የሰልጣኞች የምረቃ በዓል የአከባበር ስነስርዓት በአማረና በደመቀ ሁኔታ እንደተከበረና  ሰልጣኞቹም በበኩላቸው በዓሉ በተዘጋጀበት ስፍራ  በሞራልና በወኔ እየጨፈሩ የምረቃ በዓላቸው ያደመቁት ሲሆን፣ የትህዴን የባህል ቡድን በተለያዩ ገድላዊና ቀስቃሽ ጣዕመ  ዜማዎች እንዳቀረቡና ተመራቂዎችም በበኩላቸው የተለያዩ ግጥሞች በማቅረብ  ለበዓሉ ድምቀት ተጨማሪ ድባብ እንደፈጠሩለት የደረሰን መረጃ አመለከቷል።
     የድርጅታችን ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶምም በበዓሉ ላይ ተገኝቶ ተመራቂ ሰልጣኞች ለበርካታ ወራት ስልጠናውን በሚወስዱበት ግዜ ላጋጠማቸው ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ መሰናክሎች  በፅናትና በወኔ አልፈው ለዚህ የምረቃ በዓል መድረሳቸውን በምስጋና ከገለፀ በኋላ። አሁንም በስልጠናው ግዜ ያሳዩትን ጥንቃሬና የጀግንነት መንፈስ በተለያዩ የሰራዊት ክፍሎች ተቀላቅለው በወኔና በምሞራል በርትተው እንዲገሰግሱ በአፅንኦት ለተመራቂዎቹ መልእክቱን አስተላልፏል።
በምረቃ ስነ_ስርዓቱ ላይ የማሰልጠኛው ሃላፊ ጓድ ጎይቶም ነጋሽ ለተመራቂዎችና ለአሰልጣኞች እንኳን ለምረቃ አደረሳቹህ ካለ በኋላ ንግግሩ በመቀጠል ለተመራቂዎች አሃዱ ረመጽ በስልጠና ላይ ያሳዩትን ጽናትና ተነሻሽነት በቀጣይም ድርጅታችን በሚያሰማርቸው  ስራ ላይ ብንቃትና በትኩረት የድርጅታቸው አላማ ከግቡ እንዲደርሱ መልእክቱን እንዳስተላለፈ ከማሰልጠኛው ሪፖርተራችን አስታውቋል።

   ይህ በእንዲህ እንዳለ- ሰልጣኞቹ በበኩላቸው ለበርካታ ወራት የተሰጣቸውን ሁለተናዊ ስልጠና ጨርሰው ለዚህ የምረቃ በዓል መድረሳቸውን በደስታ በመግለፅ። የነበረውን ስልጠናም በሚገባ እንደተከታተሉና በአሁኑ ሰዓት በወታደራዊ ታክቲክና በአካል ብቃት እንዲሁም የፖለቲካዊ አቅማቸው በአስተማማኝ ሁኔታ ተገንብቶ እንደሚገኝ አስታውቀው። ከዚህ ማሰልጠኛ እንደወጡም በህዝብና በድርጅቱ  የተሰጣቸውን  አደራና ያነገቡትን ህዝባዊ አላማ ለማሳካት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ተቀን እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
የተከበራቹህ ተከታታዮቻችን ሙሉውን የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ዝርዝር ይዘት በቀጣይ ፕሮግራማችን ይዘን እንደምንቀርብ እናሳውቃለን።