Friday, May 23, 2014

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ታሕታይ ማይ ጨው ወረዳ ማይ አፅሚ ቀበሌ የሚገኝ ህዝባችን ሳይፈልግ በግድ ማዳበርያ እንዲወስድ እየተገደደ እንዳለና አንወስድም ላሉት ደግሞ እየታሰሩ እንዳሉ ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት የማይ አፅሚ ቀበሌ ነዋሪ ህዝብ በስርዓቱ ካድሬዎች በሓይል ማዳበርያ እንዲወስድ ከተደረገ በኋላ የወሰዱትን የማዳበርያ እዳ መክፈል ያልቻሉትና የህወሃት ድርጅት አባል ያልሆኑትን ለስድስት ወር አክሱም በሚገኘው እስር ቤት እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ሲሆን እነዚህ በእስር ቤት እየተሰቃዩ ካሉት ወገኖቻችን መካከልም።
1.  ተክላይ ገ/መድህን
2.  ተወለ መንገሻ
3.  ሃለቃ ገ/ምካኤል በርሀ
4.  ተስፋይ ደምለው
5.  ለኣከ ሓሳቡ
6.  አብረሃ ገ/መድህንና ሌሎችም ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ 1310 ብር የማዳበርያ እዳ የከፈለ ከእስር ቤቱ የሚወጣ ሲሆን ይህንን መክፈል ያልቻለ ግን በእስር ቤቱ ለስቃይና ለመከራ ተዳርጎ እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ አመለከተ።