Sunday, June 1, 2014

በአፋር ክልል ከበራህሌ ወደ አጉላዕ የሚወስደውን መንገድ በኩንትራት እየሰራ ያለው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት በውስጡ ተቀጥረው የሚሰሩ የቀን ሰራተኞች ግንቦት 20/2006 ዓ/ም ተቃውሞ እንዳስነሱ ታወቀ።


በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአፋር ክልል በራህሌ ወረዳ የመንገድ ስራ ኮንትራት ይዞ እየሰራ ያለው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ግንቦት 20/2006/ዓ/ም በድርጅቱ ውስጥ ተቀጥረው ለሚሰሩ ሰራተኞች ሌትና ቀን እያስገደዱ እንዲሰሩ እያደርጓቸው ስላሉ ሰራተኞቹ በበኩላቸው ግንቦት 20 የኛም በዓል አይደለም ወይ? ለምንድን ነው አስገድዳችሁ እንድንሰራ እያደረጋችሁ ያላችሁ በማለት ስለተቃወሙ የኮንስትራክሽኑ ዋና ስራስኪያጅ  ኢንጅነር ዘመንፈስና ሻለቃ ፀጋይ ለሰራተኞቹ በመሰብሰብ አሰርዋቸው ስለተባልን ነው። በግንቦት 20 በአል ላይ ሰራተኞቻችን እንድትሰሩ አላመንበትም ሲሉ ለሰራተኞቹ እንደተናገሯቸው ተገለፀ።
  በአካባቢው የሚኖር ህዝብ የቀን ስራ መጀመርያ ለኛ ነው መሰጠት ያለበት ስለዚህ ሰርተን እንድንበላ በዚህ ስራ አስገቡን ብለው ወደ ወረዳው አስተዳዳሪና ወደ መከላከያ ኮንስትራክሽን ስራስኪያጅ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆኑም የሚሰማቸው እንዳላገኙና በቅድምያ ከሌላ አካባቢና ክልል የመጡ ሰዎች ተቀጥረው እየሰሩ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
  ይህ በእንዲህ እንዳለ ለመንገዱ መስርያ ተብሎ እቤታቸው የፈረሰባቸውና የእርሻ መሬታቸው የተወሰደባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች መጀመርያ ላይ ካሳ ይሰጣችኋል ተብለው ቢነገራቸውም እስካሁን ግን የት ወደቁ ብሎ የሚያያቸው አጥተው ለከባድ አደጋ ተጋልጠው እንዳሉና በዚህ የተቆጡ የበራህሌና ሳባ ነዋሪዎችም ግንቦት 9/2006 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የፕሮጀክቱ ስራ እንዳይሰራ አስቁመውት እንደዋሉ ምንጮቻችን አክልው አስርድተዋል።