በአዊ ዞን ከሚያዝያ
18 / 2006 ዓ/ም ጀምሮ ከክልልና ከዞኖች የተወጣጡ አመራሮች ለስምንት ቀናት ሁለንትናዊ የምርጫ ቅስቀሳ እያካየዱ ቢሆኑም የወረዳዎቹ ህዝብ ግን በስልጣን ላይ ያለው ስርአት እስካሁን
ድረስ መሰረተ ልማት ሳያሟላ ቆይቶ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል ለህዝቡ አሳቢ በመምሰል እያደረገው ያለ ሽርጉድ በህዝቡ ዘንድ
ተቃውሞ እያስነሳ መሆኑ ታውቋል።
በአዊ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ያሉት መንገዶች ጥራት የሌላቸው መሆናቸውን
የገለፀው መረጃው በተለይ ከኮሶ በር እስከ ጃዊ፤ ከከሳ እስከ አየሁና ከቲሊሊ እስከ ሰከላ ያለው መንገድ የተበላሸ በመሆኑ የአከባቢው
ህዝብ በክረምት ወቅት እንደሚቸገር ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዞኑ የንፁህ ውሃ መጠጥ ባለመኖሩ ምክንያት ጥራቱ
ካልጠበቀ የጉድጓድ ውበ በመጠቀም በውሃ ወለድ በሽታዎች እየተጠቁ ካሉ ወረዳዎችም ጃዊ፤ ዚገም፤ አንከሻና እንጅባራ መሆናቸውን መረጃው
አክሎ አስረድተዋል።