Thursday, May 8, 2014

በትግራይ ማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ዓዲ ፍታው ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎችን የት.ህ.ዴ.ን ተባባሪዎችና ደጋፊዎች ናችሁ ተብለው ብእስር ቤት ታጉረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



እነዚህ የዓዲፍታው ቀበሌ ነዋሪዎች የሆኑት ዜጎቻችን የት,ህ.ዴ.ን ደጋፊዎችና ተባባሪዎች ናችሁ ተብለው ማይ ጭጎኖ በተሰኘ እስርቤት ታስረው እየተሰቃዩ እንዳሉ የገለፀው መረጃው ከታሰሩት ዜጎቻችን መካከልም አቶ ገብረአበዝጊ ተክለሃይማኖት፤ አቶ ገብረስላሴ ተክላይ፤ አቶ ገብረሚኬኤል ገብረክርስቶስና ሌሎችም መሆናቸው ታውቋል።
     መረጃው በማስከተልም እነዚህ ንፁሃን ዜጎቻችን በአሉቧልታ ወሬ እየተፈረጁ  ወደ እስርቤት እየታጎሩ ያሉትን ወገኖቻችን የወያኔ ስርአት ካድሬና የምልሻ ሃላፊ በሆነው ነጋሲ ገብረመድህንና  ምክትሉ አቶ መጋል ምክንያት እንደሆነ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።
    በተመሳሳይ ከወረዳው ሳንወጣ የዓዲፍታው ቀበሌ አስተዳዳሪዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች ያለፍላጎታቸው ለአንድ አርሶ-አደር ሁለት ኩንታል ማዳበርያ እንዲወስድ በማስገደድ ወዳልተፈለገ እዳ እያስገቡት መሆናቸውና ህዝቡም ምሬቱን በመግለፅ ላይ እንዳለ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።