Tuesday, May 13, 2014

በሁሉም የትግራይ ዞኖች በወያኔ ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለ-ስልጣናት እየተካሄደ ያለው አስመሳይ ስብሰባ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው የተገኘው መረጃ አመለከተ።



    እነዚህ የህዝብን ትክሻ እንደድልድይ ተጠቅመው ስልጣንን ሙጥኝ ያሉ የወያኔ ኢህአዴግ ባለ-ስልጣናት በሁሉም የትግራይ ዞኖች እየተዘዋወሩ ህዝብ ለማታለል ስብሰባ ያካሄዱ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በስብሰባው ተካፋይ የነበረው ህዝብ ግን ለ23 አመት ሙሉ የት ወደቃችሁ? እንዴት ናችሁ ?ብላችሁን የማታውቁ ዛሬ ልንክሳችሁ መጥተናል ማለታችሁ በህብረተሰቡ ላይ ያላችሁን ንቀት የሚያመላክት ነው እንዳልዋቸው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
    በስብሰባው ላይ ተካፋይ የነበሩ ወገኖች በስርዓቱ ላይ ያለውን ችግር ሲገልፁ መልካም አስተዳደር የለም፤ ስራ በቤተሰብና በዘመድ ሁኗል በጦርነት ግዜ አካላቸውን የጎደሉ ወገኖች ተረስተዋል የሚሉና ሌሎችን ጥያቄዎች ባነሱበት ግዜ ስብሰባውን ይመሩት የነበሩ የአዲስ አበባ ቡድን ተብለው የሚታወቁት የህወሓት ባለስልጣናት ስዩም መስፍን፤ ሰብሃት ነጋ፤ ፀጋይ በርሄ፤ አባይ ፀሐየና  ሌሎችም ባለስልጣናት በህዝቡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ጉድለታችንን እናስተካክላለን በማለት የማይተገበር መሰሪ ምላሽ እንደሰጡ ለማወቅ ተችሏል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ የስርዓቱ ከፍተኛ ባለ-ስልጣናት በተለየ መንገድ ለሽሬ ከተማ ነዋሪዎች ስብሰባ ቢያካሂዱም በስብሰባው ላይ ለቀረበው ሃሳብ ግን ህዝቡ እንዳልተቀበለውና የነበረው ስብሰባም ያለምንም ፍሬ መበተኑን በመግለፅ ስብሰባ የተጠራበት ቀንም ህዝቡ ፀሎት በሚያደርግበት ሃይማነታዊ በአል በሚከበርበት የፋሲካ ዋዜማ ህዝቡ ወደ ስብሰባ እንዲወጣ ማስገደዳቸው የህዝብ ተቃወሞ እንደገጠማቸው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።