Wednesday, May 21, 2014

የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓትን የተቃወሙ አራት የወታደር አባላት በዚህ ሳምንት ወደጎረቤት ሃገር ኤርትራ በሰላም እንደገቡ ታወቀ።



የህወሓት ኢህአዴግን ስርዓት ጠልተው ወደ ኤርትራ የገቡ ወታደሮች
1.  የሃምሳ አለቃ ሃይለ ዮሃንስ ገ/ መድህን በ22ኛ ክፍለጦር የ7ኛ ሬጅመንት የፀረ ስለያ ጋንታ አዛዥ የነበረ፣
2.  ገ/ሄር ኪዳነ ገ/ማርያም በ43ኛ ክፍለጦር የተዋጊ ማሃንዲስ አባል የነበረ፣
3.  ብርሃነ ፀጋይ በ25ኛ ክፍለጦር የ4ተኛ ሬጅመንት የ2ተኛ ሻምበል የ2ተኛ ሃይል የ4ኛ ጋንታ የ3ኛ ቲም አዛዥ፣
4.  ሰመተር ዑስማን ቀሊለ በ11 ክፍለ ጦር  ኣባል ክፍሊ የስለያ አባል የነበሩ ናቸው፣
  ወደ ኤርትራ በሰላም ከገቡት ወታደሮች መካከል የ22ኛ ክፍለጦር የ7ኛ ሬጅመነት የፀረ ስለያ ጋንታ አዛዥ የነበረው 50 አለቃ ሃይለ ዮሃንስ ገ/መድህን እንዳለው በሃገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በጎሳ የመከፋፈል ሂደት በሰፊው እንደሚታይና በዚህ ምክንያትም ወታደሮቹ በጅምላ እየታሰሩ እንደሚገኙ ገልጿል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ለ15 ዓመታት እንዳገለገለ ከገለፀ ብኋላ በነባሩ ሰራዊትና በአዲሱ ሰራዊት መካከል የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች አድልዎ እየፈፀሙ እንደሚገኙና የሆነ ጥቅማጥቅም በሚመጣበት ግዜም ላገለገለውና ለነባሩ ወታደር ወደ ጎን በመተው ለአዲሶችና ለነሱ ተላላኪ ለሆኑት ስለሚመለምሏቸው በነባሩ ሰራዊትና በሰራዊቱ አመራሮች መካከል አለመረዳዳት ተፍጥሮ እንዳለ ጨምሮ አስረድቷል።
     የ43ኛ ክፍለጦር ተዋጊ መሃንዲስ የነበረ ገብረእዝአብሄር ኪዳነ ገ/ማርያም በበኩሉ የኢትዮጵያ ሰራዊት በጎሳዊ ግጭት ውስጥ እንደሚገኝና ኦሮሞ ለኦሮሞ ትግሬ ለትግሬ የሚደጋገፉበትና በአመራር ላይ ያሉት የሰራዊት አዛዦችም ለብሄራቸው እንደሚሉ በመግለፅ በተለይ በአሁኑ ግዜ በሰራዊት ውስጥ የትግራይ ተወላጆች ብዛት ቁጥር ማነስ ችግር አጋጥሞት እንዳለ ገልጸዋል።
    ገብረእዝጊአብሄር በማስከተል በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ሰራዊት በእስር ቤት ታጉረው እንደሚገኙና እሱ ታስሮ በነበረበት እስር ቤትም የምግብና የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት እንደነበረና ለእስረኞቹ የሚደረግላቸው አያያዝም ኢ-ሰብአዊ እንደሆነ አስረድቷል።