በመረጃው መሰረት በሑመራ ከተማ 04 ቀበሌ የሚኖር ህዝብ ግፍ እየፈፀሙ ባሉት የአከባቢው የወያኔ ኢህአደግ ስርአት የፖሊስ አባላት ምሽት ላይ ተደራጅተው በሚንቀሳቀሱበት ሰአት የህብረተሰቡ አባላት እየደበደቧቸው
እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
በስርአቱ የፖሊስ አባላት መጥፎ አሰራር
የተበሳጩ ወጣቶች ግንቦት 5/2006 ዓ/ም ለግዜው ስሙ ያልታወቀ ፖሊስ አባል ተመትቶ ሆስፒታል ገብቶ እየታከመ መሆኑና ወንጀሉን
የፈፀሙት ወጣቶች በማምለጣቸው ምክንያት በአከባቢው የምትኖር አንዲት ሴት ፖሊሱን የመቱት ታውቂያቸዋለሽ ተብላ አላውቅም በማለትዋ
ምክንያት ወደ እስርቤት ወስደው እዳሰሯት የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።