የ22ኛ ክፍለጦር ክፍል በሆነችው አንድ ሬጅመንት ሰኔ 2/2006 ዓ.ም በተደረገ ስብሰባ
ላይ ሃምሳ አለቃ ምሩፅ ፍሰሃ የተባለ የፅምብላ ትግራይ ተወላጅ እኛ አንድ ሃገር የሚል አላማ ይዘን እስካሁን ክቡር የሆነችዋን
ህይወታችንን ሰጠን ስንከራተት ቆይተናል ቢሆንም ግን የመንግስት አሰራር ከግዜ ወደግዜ እየተበላሸ በመምጣት ላይ ስለሆነ ህጋዊ የሚባል
አሰራር ጠፍቶ በአመራሮች በኩል ስስት በመንገሱ በታችኛው እርከን የሚገኝ የሰራዊት አባል በአዛዦች ዘንድ ታማኝነት አጥቶ እየተበተነ
ስለሚገኝ እኔም በበኩሌ አልፈርምም ካሁን በፊት ባለማወቅ የተሳሳትኩት ይበቃኛል ብሎ ስብሰባው ላይ እንደተናገር ለማወቅ ተችሏል።
በመረጃው መሰረት ሃምሳ አለቃ ምሩፅ ፍሰሃ
በስብሰባው ላይ ብልሹ ለሆነው የመከላከያ ሰራዊት አካሄድ በነቅፈበት ጊዜ በስብሰባው ላይ የነበሩ የሰራዊት አባላት የደገፉት መሆናቸውን
የተመለከቱ ስብሰባውን ይመሩ የነበሩ የስርዓቱ ካድሬዎች በግልፅ ለገመገማቸው ወታደር ጠልፈው ወደ ማዕከላዊ ዕዝ በመውሰድ የሰወሩት
ሲሆን። ይህንን ድርጊት የሰሙ ቤተሰቦቹ ከፅንብላ ዕዙ ወደ ሚገኝበት በመሄድ ልጃችን የት ነው ያለው ልናየው ፈልገናል ብለው በጠየቋቸው
ሰዓት ለስራ ልከነዋል ልታገኙት አትችሉም የሚል ምላሽ ስለሰጧቸው ቤተሰቦቹ ስለ ልጃቸው የሚተባበራቸው የአመራር አካል ማግኘት እንዳልቻሉ
መረጃው አክሎ አስታውቋል።