Tuesday, June 17, 2014

የዓዲ-ሃገራይ ነዋሪዎች የሆኑ 4 ባለ ሃብቶች ከመከላከያ ሰራዊት መሳርያ ትገዛላችሁ በሚል ምክንያት ሰኔ 3/ 2006 ዓ/ም እንደታሰሩ ምንጮቻችን አስታወቁ።



በትግራይ ስሜናዊ ምእራብ ዞን ታሕታይ አድያቦ ወረዳ ዓዲ-ሃገራይ በህጋዊ ንግድ ስራ ተስማርተው የሚታዳደሩ ባለ ሃብቶች መሳሪያና ጥይት ከመከላከያ ሰራዊት ትገዛላችሁ እንዲሁም በኮንትሮባድ የወርቅ ማሰሻ ማሽን አስገብታችኋል። በሚል ፍትሃዊነት የሌለው ምክንያት በዓዲ-ሓገራይ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እየተሰቃዩ እንዳሉ የታሰሩትን ቤተሰብ መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
በዓዲ-ሃገራይ ታስረው እየተሰቃዩ ካሉት ዜጎቻችንም…
1.  ቐሺ በየነ
2.  አዲስ አለም አዘናው
3.  ሃፍቱ ገብረሂወትና
4.  ጉዕሽ ገብረዋህድ የተባሉ ሲሆኑ የዓዲ-ሃገራይ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ምክትል ኮማንደር አያሁነይ በበኩሉ እነዚህ ንፅሃን ዜጎች በታሰሩበት የፈጠራ ክስ ፈርተው ጉቦና ጥቅማጥቅም ቢሰጡኝ ከሚል ስስታም ባህሪው የተነሳ በልዩ ሁኔታ ይዞ እያሰቃያቸው እንዳለ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።