Wednesday, June 25, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ውስጥ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት እየፈጠረው ባለው የመሬት አስተዳደር ችግር ዜጎቻችን እርስ በርሳቸው እየተገዳደሉ እንደሆነ ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ፣፣




ምንጮቹ በሰጡት መረጃ መሰረት የወያኔ ኢህአዴግ ገዢ መንግስት በህዝቦች ላይ የተለያዩ ተንኮሎች በመፍጠር ዜጎቻችን እርስ በርሳ ቸው እንዲገዳደሉ ምክንያት እንደሆነ የገለፀው መረጃው ፍትሃዊ የመሬት አሰተዳደር ባለመኖሩ በወልቃይት ወረዳ አውራ በተባለው ጣብያ ውስጥ ግልፅ ባልሆነው የመሬት ክፍፍል በተነሳው ግጭት ምክንያት አደራጀው መልኬ የተባለው ግለ ሰብ። ለአቶ መተክያ መግደሉን ለማወቅ ተችለዋል፣፣
    ከፍፃሜው በኋላ እቶ አደራጀው መልኬ ድንገት በፈፀመው የግድያ ወንጀል ተደናግጦ ከአካባቢው የተሰወረ ሲሆን ለጠቡ መነሻ በሆኑ ያካባቢው መሬት ሸንሻኞች ለምን እንደዛ እንዳደረጉ የሚያጣራ የመንግስት አካል ባለመኖሩ በመዋቹ ቤተሰብና በገዳዩ መካከል ከፍተኛ ደም መፋሰስ እንዳጋጠመ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድተዋል፣፣ 
    ይህ ፍትሃዊ ባልሆነው በግቦና በመጠቃቀም የተመሰረተ የመሬት ሽንሸና ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሆን ብሎ ብጭፍሮቹ አማካኝነት በህዝቡ መሃል ስምምነት እንዳይፈጠር በማድረግ የስልጣኑን እድሜ ለማራዘምና በሱ ምክንያት የሚሰበሰበውን ገንዘብ ካድሬዎቹ ንሮአቸው እንዲለውጡበት እያደረገው ያለው ብልሃት ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ አስተያየታቸው እየሰጡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችለዋል፣፣