Sunday, June 15, 2014

የወያኔ ኢህአዴግ ገዢ ስርአት ተቃዋሚ ድርጅቶችን በማዳከም የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል ከዓረና ትግራይ ድርጅት ግንኝነት አላችሁ ያላቸውን 12 ወጣቶች ማሰሩን ከሽሬ ከተማ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት ሰኔ 1/ 2006 ዓ/ም የዓረና ትግራይ ድርጅት አላማውን ለማስተዋወቅ የተለያዩ መልዕክቶች የያዙ ወረቀቶችን በሽሬ ከተማ ስለበተነና ለበርካታ ሰዎች በግል ስላደላቸው ስርአቱ መጪው የምርጫ ግዜ የህዝቡን ድምፅ አጭበርብሮ ስልጣን ላይ ለመቀጠል እንዲያስችለው በማለት ለተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅት አባላት በማዳከም ስራ ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝና ከዓረና ድርጅት ግንኝነት አላችሁ በማለትም።
-    ስዩም ገብሩ
-    ዮውሃንስ ክንፈ
-    ተስፋይ በየነና ሌሎች 12 ወጣቶች የሚገኝባቸው እስር ቤት ውስጥ እንዳስገባቸው ታውቋል።
ስልጣን ላይ ያለው የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት የህዝቡን ዴሞክራሲያዊ መብት እየጠበቅኩ ነኝ በሚል ሽፋን በተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ እያካሄደው ያለው በደልና ግፍ በከፋ መንገድ እየቀጠለበት መሆኑን የሽሬ ከተማና የአካባቢው ህዝብ እንደ መነጋገርያ ነጥብ አድርገው እያነሱት መሆናቸውን ምንጮቹ አክለው አስረድተዋል።