የኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊት ውስጣዊ ሁኔታ
እጅግ በጣም እየተበላሸ በመሄድ ላይ ባለበት ሰዓት ተስፋ የቆረጡ የሰራዊት አባላት የ7 ዓመት አገልግሎት ጨርሰው ጥያቄ ቢያቀርቡም
በሰዓቱ በክብር ባለመሰናበታቸው የወታደርነት ህይወት መሯቸው በስርዓቱ ላይ ተቃውሞ እያሰሙ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው ከሰኔ
1/ 2006 ዓ/ም ጀምሮ ስርዓቱ 7እና 10 ዓመት ያገለገሉ ወታደሮች ቅነሳ በሚል ስም በቂ ያልሆነ ገንዘብ እየሰጠ እያባረራቸው
እንደሚገኝ ታወቀ።
ከመከላከያ
እየተቀነሱ ያሉ ወታደሮች ለረጅም አመታት ክቡር ህይወታችንን ቤዛ አድርገን ለመንግስት ስናገለግል ቆይተን አሁን ከትራንስፖርት ጀምሮ
ለፍጆታ የሚውሉ አላቂ ነገሮች ዋጋ ጣርያ ደርሶ ባለበት ግዜ ለማሰናበቻ የሚሰጠን ገንዘብ ለኛ የሚመጥነን አይደለም ይህ እየተሰጠን
ያለው ገንዘብም በየግዜው ለጡረታ እየተባለ ከደመወዛችን ሲቆረጥ የነበረ ነው እንጂ መንግስት ለኛ አዝኖ የሰጠን ነገር የለም በማለት
በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በስሜት እየገለፁ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ።
በተመሳሳይ ሰራዊት አነሳስታችሁ፤ እንዲፈርስ አደረጋችሁ፤ የድስፕሊን ችግርም
አሳይታችኋል ላላቸው በርከት ያሉ ወታድሮችን ያለ ምንም ማቋቋሚያ እያባረራቸው እንዳለ ታወቀ።
በመከላከያ ውስጥ ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖሩ የሰራዊት አባላትን በፍላጎታቸው
ካልሆነ እኛ ከወታደርነት ማውጣት አንችልም የሚል አሰራር እየተከተሉ እንኳን ቢቆዩም በአሁኑ ግዜ ግን አታስፈልጉንም በማለት ያለምንም
ድጎማ እያባረሯቸው ባሉበት ሰዓት ይህንን ያዩ የሰራዊት አባላትም ለኛም ልክ እንደ ጓዶቻችን ዛሬ በማታለያ ቃላት አይዟችሁ እያላችሁ
ቆይታችሁ ነገ ችግር በሚያጋጥመን ሰዓት ያለምንም እገዛ ከውትድርና አውጥታችሁ እንደምትጥሉን እናምናለን በማለት የስርዓቱን ተግባር በመቃወም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ ግርግር ተፈጥሮ
እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።