በማእከላዊ እዝ በ23ኛ ክፍለ-ጦር ተመድበው ስያገለግሉ
ቆይተው ግንቦት 30ና ሰኔ 1/2006 ዓ/ም በነበሩ ሁለት ቀናቶች ብቻ ለቀጣይ 7 አመት አገልግሎት ፈርሙ ከተባሉትና ለቀረበላቸው
ጥሪ አንቀበልም ብለው ከተቃወሙት ውስጥ ለመጥቀስ።-
- ሻምበል ካህሳይ መኮነን
- ሻምበል ክፍሎም አለማ
- ሻምበል ሓረጎት ሹሻይ ከትግራይ ብሄር
- መቶ አለቃ ካህሳይ አባሁነይ
- መቶ አለቃ ልጅአለም ታረቀ
- መቶ አለቃ ትርፉ ወንድወሰን
- መቶ አለቃ ብሩ አለማዮህ
- መቶ አለቃ ይርጋ መሰለ
- መቶ አለቃ ወርቅነህ አስረስ
- ሻምበል ወርቁ ታየ የተባሉት የሚገኙባቸውና ሌሎች ባለሌላ ማዕረግተኞች ከመከላከያ ሰራዊቱ ለቀው እንደወጡ
ውስጥ አዋቂዎችን መሰረት አድርጎ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
እነዚህ ከመከላከያ ሰራዊት የወጡ መኮንኖች አንፈርምም ብለው ላነሱት የተቃውሞ ሃሳብ በበላይ አዛዦች ተቀባይነት
ስላላገኘ ድጋፍ ስላልተሰጣቸውና በተገቢ መንገድ ሽኝት ስላልተደረገላቸው አብዛኛዎቹ የእውቶብስ ማሳፈርያ አጥተው በሽሬ፤ ሸራሮና
ሌሎችም ከተማዎች እየተንከራተቱ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
በማስከተል - ዋእላ ንህቢ በተባለው
አካባቢ የሬጅመንት አዛዥ የነበረው ሻለቃ ባህሩ እስካሁን ያገለገልኩት ይበቃኛል ወደ አገሬ እሄዳሎሁ ብሎ በተቃወመበት ሰዓት አትሄድም
ማን ይመራልሃል ብለው እንዳሰሩትና አዛዦቹም ሲመራቸው ለነበሩ የረጅመንትዋ አባላት ሰብስበው ሻለቃ ባህሩን ያሰርንበት ምክንያት
ለናንተ ተብሎ ወጪ የተደረገ በጀት ሰለሰረቀው ነው ብለው ጥላሸት በመቀባት እያነሳስዋቸው እንደሆነ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።