Monday, June 9, 2014

የትህዴን የህክምና ክፍል ለሁለት ወር ያህል በህክምና ሞያ ስያሰለጥናቸው የቆዩ ተማሪዎችን ግንቦት 18/2006 ዓ/ም አስመረቀ።




የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ / ትህዴን / ሁሌ ራሱን ለመቻልና አቅሙን ለማሳደግ እንደሚያደርገው ሁሉ በህክምና ክፍል ያለው ሁኔታም ይበልጥ በአቅም ለማጠናከር ሲል ድርጅቱ ገና ሲመሰረት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በትግላችን ወዳጆችና ደጋፊዎች እየታገዘ በየመድረኩ በርከት ያሉ የህክምና ሞያተኞች እያሰለጠነ በተግባርዊ ስራ ሲያሰማራቸው እንደቆየ ታውቋል።
    በምረቃው ስነስርአት ላይ የተገኘው የትህዴን አመራር ታጋይ ግደይ አሰፋ ለተመራቂዎች እንኳን አደረሳችሁ ካለ በኋላ የጤና ባለሞያ የሰው ሂወት በማትረፍ ትልቅ ሃላፊነት ያለው የስራ ዘርፍ ነው። ስለሆነም ይህንን ከባድ ሃላፊነት ለመወጣትና የተሰጣችሁን አደራ በተገቢ መንገድ ለማስፈፀም ከተሰጣችሁ ትምህርት በላይ የራሳችሁ የሆነ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ይጠይቃልና ህዝባዊና ድርጅታዊ ተልእኮውን ለማስፈጸም ጥረታችሁን ማሳደግ ይገባችኋል በማለት ንግግሩን እንዳሰማ ለማወቅ ተችለዋል።
    ለተመራቂዎች የሞያ ስልጠና ሲሰጥ  ከነበሩት ታጋይ ገብረመድህን አለማዮህ የትህዴን የህክምና ክፍል በቀጣይ እድገት ላይ ይገኛል ካለ በኋላ እናንተ ተመራቂዎች የሱ አካል ናቹህ እና በዚህ ማጠናከርያ ስልጠና (ሪፍረሽ ኮርስ) በሚል በተሰጣቹህ ስልጠና  ያሳይችሁት ተነሻሻነት በስራ  ላይ ስትሰማሩ በተግባር እንደምትተረጉሙት እምነታችን ነው ሲል መልእክቱን አስተላልፏል።
ይህ በእንዲህ እያለ ተመራቂዎችን በመወከል መልእክቱን ያስተላለፈ ታጋይ ታሪኩ ገብረእዝጊአብሄር በምረቃው ላይ ለተገኙ ታጋዮችና አመራሮች እንኳን በደህና መጣቹህ በማለት ለሁለት ወራት ያክል የተሰጠ የህክምና ሞያ ስልጠና ሰልጣኞችን በምሉ አቕማቸው ሊያሰራ የሚችል አቅም እንደያዙ ይህ ተማሪዎቹ በትምህርቱ ላይ በነበራቸው ፍላኦትና ተነሻሻነት ሆኖ በይበልጥ ደግሞ ውጤቱ የመመህራኑ ጥረት መሆኑን አስረድቷል።
በተጨማሪ የቀሰሙት የህክምና ሞያ ትምህርት ለስራቸው ብቃት የሚያሳድግ እድል ለከፈተላቸው ለድርጅታቸውና ለአመራሩ በማመስገን ብድርጅቱ ለተሰጣቸው ከባድ ሞያዊ አደራ ከግቡ ለማድረስ ለይት ተቀን እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
    በመጨረሻ  ከፍተኛ ውጤት ላመጡት ተማሪዎችና በማሰልጠን ላይ ለነበሩ መምህራን። በስልጠናው መመረቅያ ቀን በነበሩ ከትህዴን የበላይ አመራሮች እጅ ሽልማት የተቀበሉ ሲሆን በባአሉ ወቅትም የትሃዴን የባህል ቡድን ተገኝታ የተለያዩ ጣእመ ዜማዎችና ድራማዎችን ማቅረብዋን ዘገባው ጨምሮ አስታውቀዋል።