በመረጃው መሰረት አቶ ተክለ ሞጎስ የተባለ የአበባ የውሃንስ ቀበሌ አስተዳደር ከ250 ኩንታል በላይ
እህል ለግል ጥቅሙ በማዋሉ ምክንያት የተቆጡ የቀበሌው ነዋሪዎች ፍትህ ለማግኘት ወደ ወረዳው አስተዳደር እሮሮአቸውን ባቀረቡለት
ግዜ የወረዳዋ አስተዳዳሪ ለማስመሰል የሚያጣሩ ሰዎች ልኬላቸዋለሁ በማለት እንደመለሰላቸው ታውቋል።
በቀበሌው አስተዳደሪ የተሰረቀ የእርዳታ እህል ሊያጣሩ የተላኩ ሰዎች
የወረዳው የፀጥታ ሃላፊ ደስታ ወልደሃዋሪያትና የካቢኔ አባል አቶ ገብረስላሴ ገብረዋህድ ሲሆኑ ግንቦት 20/ 2006 ዓ/ም ህዝብ
ሰብስበው ባደረጉት ማጣራት እህሉ በቀበሌው አስተዳደር እንደተሰረቀ በመረጃ ተረጋግጦ እያለ እስከ አሁን ግን ወንጀለኛው የተወሰደበት
እርምጃ ባለመኖሩ ምክንያት ህዝብ ምሬቱን እያሰማ እንዳለ ለማወቅ ተችለዋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ ምሬቱን እያሰማ ላለው ህዝብ ለማረጋጋት ሲል ነዋሪዎችን
ሰብስቦ ባደረገው ንግግር “ ከዚህ በፊት የሰራችሁት 800,000 (ስምንት መቶ ሺ) እከፍላችኃለሁ እስከ አሁን ያልሰጠኋችሁ ምክንያት
ከክልል ስላልተላከ ነው። “ በማለት የስብሰባውን ትኩረት መቀየሩ በእህሉ ስርቆት እጁ ስላለበት እንዳይጋለጥ በመስጋት እንደሆነ
የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።