Sunday, June 15, 2014

በአምቦ ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ ህዝብን አነሳሳታችኋል በሚል ግንቦት 27/2006 ዓ/ም በኢህ.አ.ዴ.ግ የፀጥታ ሃይሎች ታፍነው የተወሰዱ ንፁሃን ዜጎች ለሞትና ለስቃይ ተጋልጠው እንዳሉ ታወቀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአምቦ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ንፁሃን ወገኖች ህዝቡን ለተቃውሞ አነሳሳታችኋል ተብለው 150 ሰዎች ታፍነው እንደተወሰዱና ከእነሱ ውስጥም 17 ሰዎች እንደሞቱና የቀሩትም በደብረዘይት ልዩ ስሙ ቢሾፍቱ በተባለ ቦታ ታስረው እንደሚገኙና ዘመድ ወዳጅና ቤተሰብ ለማየት የማይፈቀድ መሆኑንም ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልፀዋል።
      በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ግምቢ ከተማ መጪ መንደር በተባለ አካባቢ ባለፈው ጊዜ በተካሄደ ተቃውሞ ተሳታፊና አነሳሾች ናችሁ በማለት ግንቦት 7 2006 ዓ/ም በስርዓቱ ተላላኪዎች አማካኝነት ሃኒ መላኩ የምትባል ሴት የምትገኝበት 35 ንፁሃን ወገኖች ታፍነው እንደተወሰዱና እስካሁን ድረስ  የት እንዳሉ የሚያውቅ ቤተሰብም ይሁን ዘመድ እንደሌለና በአጠቃላይ በአካባቢው የሚገኙ ህዝቦች በገዥው ስርዓት የጸጥታ ሓይሎችና ከድሬዎች ከባድ ግርፋትና የማስፈራራት ዛቻ እየደረሳቸው እንደሚገኙ ለማውቅ ተችሏል።