ከ10 እስከ 15 ዓመታት
በሱዳን ሃገር ሲኖሩ የቆዩና ለአመታት ያፈሩትን ንብረትና የተለያዩ መሳሪያ ይዘው ወደ ሃገራቸው እየገቡ ባሉበት ሰዓት ልጉዲ በሚገኘው
ኬላ ላይ ስርአቱ ህጋዊ መቀበያ ካርድ የሌለውን ቀረፅ በመስጠት እንዲከፍሉ እያስገደዳቸው መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።
እነዚህ ዜጎች እንዲከፍሉ ከሚገደዱት ቀረፅ።-
Ø ለአንድ ቴሌቪዥን 1600 ብር
Ø ለአንድ ፍሪጅ 2400 ብር
Ø ለአንድ የቤት አልጋ 200 ብር ወዘተ እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆናቸው ታወቀ።
ከእነዚህ
ንብረታቸውን ይዘው ከመጡ ተመላሾችና መክፈል አንችልም ብለው ንብረታቸው ኬላ ላይ ከተወሰደባቸው ወገኖች መካከል አስካለ ሃጎስ የተባለች የተምቤን ተወላጅ በሁለት መኪና ጭናው ካመጣችው ንብረት
ግማሽ መኪና የሚሆነውን በቀረፅ አሳበው የስርዓቱ ተላላኪዎች እንደወሰዱት
መረጃው ዋቢ አድርጎ በመጥቀስ አስረድቷል።