Wednesday, June 11, 2014

ከግንቦት 29 /2006 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች የአሸባሪዎች ደጋፊዎችና ተባባሪዎች ናችሁ እየተባሉ በስርአቱ ታፍሰው ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች እየተወስዱ መሆናቸው ታወቀ።



    የወያኔ ኢ.ህ.አ.ደ.ግ ስርአት ልክ እንደ1997 ዓ/ም የሚመሳሰል ወንጀል ያልፈፀሙ ወገኖችን አሸባሪዎች፤ ደጋፊዎችና ተባባሪዎች የሚል ምክንያት እየፈጠረ በማሰር ላይ እንደሚገኝ የገለፀው ይህ መረጃ በተለይም በአዲስ አበባ ተክለሃይማኖት ክፍለ ከተማ ወጣቶች በብዛት እየታፈሱ ወደ ዝዋይና ሹዋሮቢት ተወሰደው እየታሰሩ መሆናቸው ተገለፀ።
    ከታሰሩት ወጣቶች ለመጥቀስ ያክልም መቕደስ ሃይሉ፤ ቴድሮስ ባይነሳይ፤ ተሾመና ሌሎች የሚገኙባቸው ወጣቶች ሲሆኑ የታሰሩ ቤተሰቦችም ንፁሃን ልጆቻችን ታሰሩብን በማለት  እምባ ጠባቂ ወደ ተባለ ድርጅት  አቤቱታቸውን ባቀረቡበትም ግዜ የምናውቀው ነገር የለም መንግስትን ሂዳችሁ ጠይቁ ብለው እንደመለሷቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።