Wednesday, June 11, 2014

በሱዳን ሃገር ተሰድደው ለአመታት ሲኖሩ የቆዩ ወገኖች ወደ ሃገራቸው እየተመለሱ ባሉበት ጊዜ ይዘውት ለሚገቡት መሳሪያና ንብረታቸው ቀረፅ እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።



ከ10 እስከ 15 ዓመታት በሱዳን ሃገር ሲኖሩ የቆዩና ለአመታት ያፈሩትን ንብረትና የተለያዩ መሳሪያ ይዘው ወደ ሃገራቸው እየገቡ ባሉበት ሰዓት ልጉዲ በሚገኘው ኬላ የኢትዮጵያ መንግስት ህጋዊ መቀበያ ካርድ የሌለውን ቀረፅ በመስጠት እንዲከፍሉ እያስገደዳቸው መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።
እነዚህ ዜጎች ኣንዲከፍሉ ከሚገደዱት ቀረፅ።-
Ø ለአንድ ቴሌቪዥን 1600 ብር
Ø ለአንድ ፍሪጅ 2400 ብር
Ø ለአንድ የቤት አልጋ 200 ብር ወዘተ እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆናቸው ታወቀ፣
   ከእነዚህ ንብረታቸውን ይዘው ከመጡ ተመላሾችና መክፈል አልችልም ብለው ንብረታቸው ኬላ ላይ ከቀረባቸው ወገኖች መካከል  አስካሌ ሃጎስ የተባለች የተምቤን ተወላጅ በሁለት መኪና ጭናው ካመጣችው ንብረት ግማሽ መኪና የሚሆነውን በቀረፅ አስበው የስርዓቱ ተላላኪዎች  እንደወሰዱት መረጃው ዋቢ አድርጎ በመጥቀስ አስረድቷል።