በምንጮቻችን መረጃ መሰረት እነዚህ ግንቦት 22/ 2006 ዓ/ም ከጎንደር ወደ ዳንሻ በሚወስደው መንገድ
ልዩ ስሙ ማይ ደሌ በሚባለው ቦታ የተገደሉ የኬላ ጠባቂ ታጣቂ የፖሊስ አባል ዋና ሳጂን አሸብር አስራት፤ሚሊሻ ሞገስ ይርሳውና ሚሊሻ
ጌቱ መኩሪያ የተባሉት መሆናቸው ታውቋል።
ሦስቱ የኬላ ጠባቂ ታጣቂዎችን በአውቶማቲክ
ጥይት ተኩሶ ሊገድል የቻለ የጉሙዝ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆነ ወታደር በምዕራብ ዕዝ 5ኛ ሜካናይዝድ ውስጥ በእርሱና በሌሎች ጓደኞቹ
ላይ ይፈፀም የነበረው አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ አድሎዎ ሊቋቋመው ባለመቻሉ እንደሆነና በዚህም ምክንያት ከነሙሉ ትጥቁ ወደ ትውልድ ቦታው እየተጓዘ በነበረበት ጊዜ ማይ ደሌ በተባለው ቦታ ጥበቃ
ላይ የነበሩ የኬላ ሰራተኞች ሊያቆሙት በሞከሩበትና ትጥቅህ አውርድ ባሉበት ሰአት ተኩሶ እንደገደላቸው ለማወቅ ተችለዋል።
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ
መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያለው የተበላሸ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ልዩነት
የፈጠረው መከፋፈል አብዛኛዎቹ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የገዥውን መንግስት ግፍ ሊቋቋሙት ባለመቻላቸው እግራቸው ወወደመራቸው እንደሚጠፉና
በርካታዎች ደግሞ የትጥቅ ትግል ወደ ሚያካሂዱ ድርጅቶች እየገቡ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።